ሽርክ
ሽርክ (ማጋራት) ለአላህ ብቻ ከሚገቡ ነገሮች አንዱንም ቢሆን ከሱ ውጪ ለሆነ ፍጡር ማድረግ በመሆኑ የተውሂድ ተቃራኒ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَاعْبُدُوا
اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا
“አላህንም ተገዙ በርሱም ምንንም አታጋሩ” (አን ኒሳእ 36)
ሽርክ ከኃጢአቶች ሁሉ የከፋ ከበደሎቸ ሁሉ የላቀ ሲሆን አንድ ሰው ንሰሀ ሳይገባ በሽርክ ላይ እንዳለ ከሞተ ኃጢአቱ የማይማርና ጀነት እርም የሆነበት ሆኖ ጀሀነም ውስጥ ይዘወትራል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
إِنَّ
الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ
“ማጋራት ታላቅ በደል ነው” (ሉቅማን 13)
إِنَّ
اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن
يَشَاءُ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَى إِثْمًا عَظِيمًا
“አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኃጢአት በእርግጥ ቀጠፈ::” (አል ኒሳህ 48)
إِنَّ
اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَلِكَ لِمَن
يَشَاءُ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا
“አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከውነት) የራቀን ጥመት በእርግጥ ጠመመ” (አን ኒሳእ 116)
إِنَّهُ
مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ
النَّارُ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ
“እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ:: መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም::” (አል ማአዳህ 72)
ሽርክ በሁለት ይከፈላል፦
1ትልቁና
2ትንሹ
1ኛ. ትልቁ ሽርክ፡-
ለአላህ ቢጤ በማድረግ ልክ እንደርሱ ማምለክ ሲሆን ይህ ከእስልምና የሚያስወጣና መልካም ስራን በአጠቃላይ የሚያበላሽ ተግባር ነው፡፡ ይህን ድርጊት ፈፃሚ በዚህ ሁኔታ ከሞተ ጀሀነም ውስጥ ዝንተ አለም ይዘወትራል፡፡ ሞቶ አያልቅለትም ቅጣትም አይቀልለትም፡፡
የትልቁ ሽርክ አይነቶች
ትልቁ ሽርክ አራት አይነት ነው፦
1. በልመና ማጋራት፡-
ልመና
ከታላላቅ የአምልኮ ዘርፎች አንዱ ነው፡፡ እንዲያውም የአምልኮ ዋናው ክፍል ነው፡፡ ነብዩ እንዲህ ይላሉ ‹‹ዱዓዕ የዒባዳ ዋናው ነው›› አላህም እንዲህ ብሏል
وَقَالَ
رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ
عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ
‹‹ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡›› (አል ጋፊር 6ዐ)
ዱዓእ
አምልኮ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ከአላህ ሌላ ለሆነ ፍጡር ማድረጉ ሽርክ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ነብይን፣ መልአክን፣ ወልይን፣ ቀብርን፣ ድንጋይንና ማንኛውንም ፍጡር የለመነ አጋሪ ከሃዲ ይሆናል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፦
‹‹ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡›› (ሙእሙኑን 11)
ዱዓእ አምልኮ ስለመሆኑና ከአላህ ውጭ ለሆነ ማድረግ ሽርክ እንደሚሆን ከማስረጃዎች ውስጥ እንዲህ የሚለው የአላህ ቃል አንዱ ነው፡፡
‹‹በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡›› (አንከቡት 65)
እነዚህ
አጋሪዎች ሲመቻቸው እንደሚያጋሩና ሲቸግራቸውና ሲጠባቸው ግን ዒባዳን ለአላህ ብቻ እንደሚያደርጉ ተናገረ፡፡ ታዲያ ሁሌ በድሎትም በችግርም በአላህ ላይ የሚያጋራ እንዴት ሊሆን ነው? አላህ ይጠብቀን፡፡
2 በፍላጐትና የኒያ ማጋራት፡-
ማለት በሚሰራው ስራ ዱንያን ወይም ልክ እንደሙናፊቆች ሙሉ በሙሉ ለይዩልኝና ይስሙልኝ ብቻ መስራትና የአላህን ፊትና የአኺራን ሀገር አለመፈለግ፡፡ ይህ ትልቁ ሽርክ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦
‹‹ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) በእርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን፡፡ እነሱም በርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም፡፡ እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው፡፡ የሠሩትም ሥራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ፡፡ (በቅርቢቱ ዓለም) ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው፡፡›› (ሁድ 15-16)
ይህ የሽርክ አይነት ስውር የሆነና አደገኝነቱ የከፋ ነው፡፡
3 በትዕዛዝ ማጋራት፡-
አንድ
ሰውን አላህ የፈቀደውን ሲከለክልና አላህ የከለከለውን ሲፈቅድ መታዘዝ እንዲሁም ሰዎች ሀላልና ሀራም ማድረግ እንደሚችሉና በዚህ ላይ እነሱን መታዘዝ እንደሚቻል ማመን ማለት ነው::ይህ ተግባር እስላምናን ሀይማኖት እንደሚጋጭ እያወቀ ይህን የሚያደርግን የሚታዘዝ አዛዡን ሰው የአላህ ቢጤ አድርጓል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ትልቁን ሽርክ ፈፃሚ ነው፡፡አላህ እንዲህ ይላል፦
اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ
وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا
أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَهًا وَاحِدًا لَّا إِلَهَ إِلَّا هُوَ
سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ
‹‹ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡›› (አል ተውባህ 31)
የዚህ
አንቀፅ ትርጓሜ፡- ዑለማዎችንና ባህታዊያንን በኃጢአት መታዘዝ ማለት እንጂ እነርሱን መለመን ማለት እንዳልሆነ ነብዩ አብራርተዋል፡፡ ዓዲይ ኢብኑ ሃቲም ለነቢዩ “እኛኮ ስናመልካቸው አልነበረም” ሲላቸው እንዲህ በማለት እነርሱን ማምለክ ማለት የአላህን ህግ በመቀየር በወንጀል ሲያዙ ትዕዛዛቸውን መቀበል ማለት እንደሆነ ገለፁለት “አላህ ሀላል ያደረገውን ሲከለክሏችሁ እናንተ ትታዛቿቸው አልነበረምን? አላህ እርም ያደረገውን ደግሞ ሲፈቅዱ እነርሱን በመታዘዝ የተፈቀደ ታደርጉ አልነበርን? “እንዴታ” ሲላቸው እነርሱን ማምለክ ማለት ይኸው ነው አሉት፡፡››
4. በውዴታ ማጋራት፡-
ማክበር፣
ማላቅ፣መዋረድና መተናነስን የሚያስከትል ለአላህ እንጂ የማይገባን ውዴታ ለፍጡር ማድረግ ትልቁ ሽርክ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦
وَمِنَ
النَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ اللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ
اللَّهِ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ
‹‹ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡›› (አል በቀራህ 165)
2ኛ. ሁለተኛው የሽርክ አይነት ትንሹ ሽርክ ነው፦
ትንሹ
ሽርክ ማለት ማንኛውም ወደ ትልቁ ሽርክ መዳረሻ መንገድ የሆነ ወይም ደግሞ ሸሪዓዊ ጥቅሶች ላይ ሽርክ ተብሎ የተሰየመና ነገር ግን የትልቁን ሽርክ መጠን ያልደረሰ ሲሆን ነው፡፡ ይህ ሽርክ በስራዎች ሁኔታና በምላስ ንግግር የሚከሰት ሲሆን ሸሪዓዊ ብይኑ ይህን የሰራ ሰው ልክ እንደ ትላልቅ ወንጀሎች ፈፃሚ በአላህ ፈላጐት ስር ይሆናል፡፡
ለትንሹ ሽርክ ምሳሌ ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች፦
ሀ. ትንሹ “ሪያእ” (ለይዩልኝ መስራት)፡-
ለዚህ ማስረጃው ኢማም አህመድና ሌሎችም ከነብዩ የዘገቡት የሚከተለው ሀዲስ ነው፦
‹‹እናንተ ላይ ከምፈራው ሁሉ የከፋው ትንሹ ሽርክ ነው፡፡ ሰሃቦችም “ትንሹ ሽርክ ምንድ ነው?” ሲሉ ነብዩም “መልካም ስራን ለይዩልኝ መስራት ነው”
የትንሳኤው
እለት አላህ ለሰዎች ምንዳን ሲሰጥ ለይዩልኝ ሚሰሩትን እንዲህ ይላቸዋል “በዱንያ ላይ እንዲያዩላችሁ የምታደርጉት የነበሩ ሰዎች ዘንድ ሂዱና እስቲ የሚሰጡዋችሁ ምንዳ ካለ እዩ፡፡”
ለ. “በአላህና በአንተ ፍላጐት…” የሚለው አባባል፡-
አቡ ዳውድ እንደዘገቡት ነብዩ እንዲህ ብለዋል ‹‹በአላህና በእገሌ ፍላጎት (ይህ ጉዳይ ተሳካልኝ) አትበሉ:: ነገር ግን አላህ ፍላጎት በኋላ እገሌም ስለሻው…… ማለት ትችላላችሁ”
መ. “አላህና እገሌ ባይኖሩ ኖሮ… ”
ወይም “ውሻ ባይኖር ሌላ ገብቶ ነበር” የመሳሰሉ ቃላቶችን መጠቀም፡፡ አቡ ሃቲም ተፍሲር መፅሐፋቸው ላይ እንደዘገቡት ኢብኑ ዓባስ ስለዚህ አንቀፅ ትርጉም እንዲህ ብለዋል ፡-
فَلَا
تَجْعَلُوا لِلَّهِ أَندَادًا وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
‹‹ቢጤ
ማለት ተጋሪ ማለት ነው፡፡ የጉንዳን ኮቴ በሌሊት ጨለማና በልሙጥ ጥቁር ድንጋይ ላይ ስውር ከሚሆነው በላይ ስውር ነው፡፡
ለምሳሌ
በአላህ በህይወትህና በህይወቴ እምላለሁ ፣ ውሻ ባይኖር ሌባ ይገባ ነበር ፣ ቤት ውስጥ ዶሮ ባይኖር ሌባ ይገባ ነበር ፣ በአላህና በአንተ ፍላጐት ፣ አላህና አንተ ባትኖሩ ኖሮ የመሳሰሉትን ቃላት መጠቀም ማለት ነው፡፡ “እገሌ” የገባበት ሁሉ ሽርክ ነው፡፡ ብለዋል››
No comments:
Post a Comment