‘ኢስባል’
ምንም እንኳን ድርጊቱ በአላህ (ሱብሃን ወታእላ) ዘንድ በጣም ከባድ ቢሆንም ብዙ ሰዎች እንደ ተራ ነገር አድርገው ከሚያዩዋቸው መካከል አንዱ ‘ኢስባል’ ነው፤ ማለትም አልባሳትን በማስረዘም ከቁርጭምጭሚት በታች አውርዶ መልበስ።
አቡዘር አል ጊፋሪ ነቢያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡-
“በፍርዱ ቀን አላህ የማያነጋግራቸው፣ የማይመለከታቸው፣ ከኋጢአታቸው የማያፀዳቸው ሶስት ዓይነት ሰዎች አሉ፡-
1,የታችኛውን ልብሱን ከቁርጭምጭሚቱ በታች አውርዶ የሚለብስ፤
2,ስጦታዎቹን ወይም የዋለውን ውለታ ለሌሎች የሚያስታውስና
3,ምርቱን በውሸት መሀላ የሚሸጥ ናቸው።” ሙስሊም ዘግበውታል
ያ እንዲህ የሚል «እኔ ልብሶቼን ከቁርጭምጭሚቴ በታች የማወርደው ከትዕቢት (ኩራት) የተነሳ አይደለም» የሚለው መከላከያ ተቀባይነት የሌለውና ራስን የማወደሻ መንገድ ነው። ይህ ትዕዛዝ የተላለፈው ለነጭም፣ ለጥቁርም፣ ለአዋቂም፣ ለአላዋቂም ነው። ምክንያቱም ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋልና፡-
“ከቁርጭምጭሚት በታች የሚሆን ማንኛውም የታችኛው የልብስ ክፍል በገሀነም ውስጥ ነው።” (አህመድ ዘግበውታል)
ሱሪን በማሳጠር በኩል ሱናው የባት/ቅልጥም ግማሽ ላይ ሲሆን እስከ ቁርጭምጭሚት ያለው ደግሞ እስካላለፈ ድረስ ችግር የለውም።
አቢ ሰዒድ አል ኹድሪይ እንዳወሩት ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል «የአንድ ሰው ሽርጡ ግማሽ ባቱ ላይ ነው። እስከ ቁርጭምጭሚቱ ችግር የለውም፣ ከሁለት ቁርጭምጭሚቱ ያሳለፈ የእሳት ነው። በኩራት መንፈስ የጎተተ ደግሞ አላህ አያየውም።» (አቡ ዳውድ ዘግበውታል)
እንግዲህ እኚህና እኚህን የመሳሰሉ የነቢዩ ሀዲሶች እንደሚያስረዱት ልብስን ከቁርጭምጭሚት በታች ማውረድ ፍፁም የማይፈቀድ ሐራም ተግባር ነው። ሆኖም ይህን ህግ ተላልፎ በመዘናጋትም ይሁን በሸይጧን ጉትጎታ ያላሳጠረ ሰውነቱ ለእሳት እንደሚዳረግ ሲየስጠነቅቁ፣ ለኩራት ብሎ የሚጎትት ደግሞ ከአላህ ዕይታ እንደሚነፈገው ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ተናግረዋል።
አላህ (ሱብሃን ወታእላ) ነቢዩን እንድንታዘዝ እና እንድንከተል አዞናል ይህን የማንፈፅም ከሆነ ግን እንደ ፊርዐውን አሳማሚ ቅጣት እንደሚጠብቀን በቁርአን አስጠንቅቋል። ምክንያቱም ነቢዩን መታዘዝ አላህን መታዘዝ ነውና። ነቢዩም የእርሳቸውን ትዕዛዝ ኡመታቸው እንዲተገብር አበክረው ተናግረዋል። የነቢዩን ቃል አክብረው ታዛዥ የሚሆኑትም ጣፋችና ዘልዐለማዊ የሆነውን የደስታ ህይወት ያለምንም ስጋት እንደሚቋደሱ አስተላልፈዋል።
ታዲያ ምን ትጠብቃለህ ጃል? ዕርጅና ወይስ ሞት?

No comments:
Post a Comment