بسم الله الرحمن الرحيم
የዓርብኛ ፊደል መውጫ ቦታዎች مخارج الحروف
ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው ። የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያችን በቤተሰባቸው በባልደረቦቻቸውና
የእነርሱን ፈለግ በመልካም በተከተሉ ሁሉ ላይ ይሁን።
መኸረጅ مخارج
መኸረጅ ማለት፦ፊደሉ ሚወጣበት ቦታና ከሌሎች የሚለይበት ማለት ነው። ይህ የፊደል መውጫ ደግሞ በሁለት ይከፈላል።እነርሱም፦
1)ፊደሉ ሚወጣበት ቦታ የታወቀ المخرج المحقق
2) ፊደሉ ሚወጣበት ቦታ ስለማይታወቅ የሚመጠን ናቸው። المخرج المقدر አንድ ፊደል ከየት
እንደሚወጣ ለማወቅ ከተፈለገ ተከታዮቹን ነገሮች በማድረግ ነው።
1ኛ ሃምዛን በማምጣት በተፈለገው የአናባቢ
ምልክት (ሃረካ) ማድረግ።
2ኛ የሚፈለገውን ፊደል "ሳኪን" ወይም "ሸዳ" በማድረግ ማወቅ ይቻላል። ምሳሌ፦ ኢፍ ኢፈ إف إف
ዑለማዎች የዓርብኛ ፊደሎች የሚወጡበትን ቦታ በተመለከተ አምስት ዋናዋና ቦታዎችን አስቀምጠዋል።
የሚከተሉት ናቸው።
1) الجوف አል ጀውፍ፡ 2) الحلق አል ሃልቅ፡
3) اللسان አሊሳን፡ 4) الشفتان አሸፈታን፡
5) الخيشوم አል ኸይሹም። 1) الجوف አል ጀውፍ ፡
ይህ ማለት ፦በአፍ ውስጥና በጉሮሮ መካከል ያለው ክፍት ቦታ ማለት ነው። ከእርሱም ሶስቱ የመሳቢያ (መድ) ፊደሎች
ይወጣሉ። እነርሱም፦
አሊፍ ሳኪን ሆኖ ቀድሞት የመጣው
"ፈትሃ" ሲሆን። ምሳሌው፡ حا ሃ ። ያ ሳኪን
ሆኖ ቀድሞት የመጣው "ከስራ" ሲሆን። ምሳሌው፦ حي ሂ ። ዋው ሳኪን ሆኖ ቀድሞት የመጣው " ደማ" ሲሆን። ምሳሌው
፦ حو ሁ ።
እነዚህ የጀውፍ ፊደሎች ተያይዘው ሲመጡ ደግሞ በሚከተለው መልኩ ነው።
(نوحيحا)
2) الحاق ጉሮሮ
ማለት ሲሆን
እርሱም ሶስት አይነት ቦታዎች አሉት ስድስት ፊደሎች ሚወጡበት።
፠ أقصى الحلق አቅሰል ሃልቅ፡ የጉሮሮ መጨረሻ ማለትም ወደ ደረት የቀረበው ቦታ ማለት ሲሆን
"ሃምዛ እና ሃ" ይወጣሉ። "أ ه"
፠ وسط الحلق ወሰጠል ሃልቅ፡ የጉሮሮ መካከል ማለት ሲሆን ከእርሱም "ዓይን እና
ሃ" ይወጣሉ። "ع ح" ፠ أدن الحلق አድነል
ሃልቅ፡ ቅርቡ የጉሮሮ ቦታ ማለትም ወደ አፍ የቀረበው ማለት ሲሆን ከእርሱም "ገይን እና ኻ" ይወጣሉ።
"غ خ"
3)اللسان አሊሳን፡
ምላስ ማለት ሲሆን አስር የመውጫ ቦታዎች
አሉት ለአስራ ስምንት ፊደሎች። እነርሱም እንደሚከተለው ይቀርባሉ።
፠ أقصى اللسان አቅሰ ሊሳን፡ ይህም
የምላስ መጨረሳ ማለት ሲሆን ከእርሱም "ቃፍ እና ካፍ" ይወጣሉ። "ق ك" የ"ቃፍ"
መውጫ ፦የምላስ መጨረሻ ማለትም ወደ ጉሮሮ የቀረበው ቦታ ከላይኛው ላንቃ ጋር በመነካካት ረጠብ ካለው ቦታ
ነው። የ"ካፍ" ም መውጫ በዚሁ መልኩ ሆኖ ነገር
ግን እርሱ ደረቅ ካለው ቦታ ነው ሚወጣው።
፠ وسط اللسان ወሰጠ ሊሳን፡-የምላስ መካከል ማለት ሲሆን ከእርሱም
"ጂም ሺን እና መሳቢያ (መድ) ያልሆነችው ያ" ይወጣሉ።
" ج ش ي"
፠ حافتة اللسان ሃፈተ ሊሳን፡ ይህ ማለት የምላስ ጎን አወጣጣቸውም የምላስ መካከል ከላይኛው
ላንቃ ጋር በመነካካት ነው።
፠ حافة اللسان ሃፈተ
ሊሳን፡ የምላስ ጎን ወይም ዙርያው ማለት ሲሆን አንድ መውጫ ቦታ አለው ለሁለት ፊደሎች። እነርሱም "ዷድ እና ላም"
ናቸው። "ض ل"
የ"ዷድ" መውጫ የምላስ ጎን ከላይኛው መንጋጋ ጋር በመነካካት(በመገናኘት) ነው። የ"ላም"
መውጫ ደግሞ ከቅርቡ የምላስ ጎን ማለትም ወደ አፍ የቀረበው ቦታ ሲሆን የሚወጣው ምላስ በውስጥ በኩል ባለው የላይኛው የጥርስ ድድ ላይ በማረፍ ነው።
እነዚህ ድድቸው የሚነኩት ጥርሶችም
የሚከተሉት ናቸው።
A
الثنيتين አሰንየተይን፦ሁለቱ የፊት ጥርሶች።
A
الرباعيتين አሩባዕየተይን፦ቀጥሎ
ያሉት ከታችም ከላይም አራቱ ጥርሶች።
A
النابين አናበይን፦ክራንቻ
ወይም የውሻ ጥርስና
A
الضاحكين አዷሂከይን፦ ከክራንቻ ጥርስ ቀጥሎ ያሉት ከላይ ሁለት ከታች ሁለት ባጠቃላይ አራቱ ጥርሶች ናቸው።
፠ طرف اللسان ጠረፈ
ሊሳን፦ የምላስ ጫፍ ማለት ሲሆን አምስት መውጫ ቦታዎች አሉት አስራ
አንድ ፊደሎች
የሚወጡበት እነርሱም የሚከተሉት ናቸው።
Ñ
"ن" "ኑን"
የምትወጣው የምላስ ጫፍ ትይዩ ሆኖ የፊት ጥርሶች የውስጥ ድድ ጋር በመነካካት ነው። ከላም መውጫ ትንሽ ወረድ ብሎ።
Ñ
"ر " "ራ"
የምትወጣው የምላስ ጫፍ ትንሽ ገልበጥ ብሎ (በስተጀርባው) የፊት ጥርሶች ድድ ጋር በመገናኘት ነው። ከ"ኑን" መውጫ
ጋር ይቀራረባል።
Ñ
"ط ت د " "ጧ
ታ ዳል" የሚወጡት የምላስ ጫፍ የፊት ጥርሶች መጀመሪያው
ወይም ድዱ አጠገብ ባለው ቦታ በማረፍ ነው።
Ñ
"ص ز س" "ሷድ ዛ ሲን " የሚወጡት የምላስ መጨረሻ ከፊት ለፊት ጥርስ ከታችኛው ወለል በውስጡ በኩል ካለው
ጋር በመነካካት በላይኛውና በታችኛው ጥርሶች መካከል ትንሽ ክፍተትን በማድረግ ነው።
Ñ
" ظ ذ ث " " ዟ ዛል ሳ " የሚወጡት ፦የምላስ ጫፍ ከላይኛው የጥርስ
ጫፍ ጋር በመነካካት ነው።
4) الشفتان አሸፈታን፦
ሁለቱ ከንፈሮች ማለት ሲሆን እርሱም
ሁለት መውጫ ቦታዎች አሉት ለአራት ፊደሎች ።የሚከተሉት ናቸው። "ፋ ሚም ባ እና መሳቢያ ያልሆነችው ዋው " "ف م ب و"
Ñ
"ፋ" የሚወጣው የፊትለፊት ጥርሶች ከታችኛው ከንፈር ከውስጡ ጋር በመገናኘት
ነው።
Ñ
"ዋው" የሚወጣው ደግሞ ሁለቱን ከንፈሮች ወደ ፊት በማምጣት ወይም በማሞጥሞጥ
ነው።
Ñ
"ሚም" የሚወጣው
፦ ሁለቱን ከንፈሮች
በማጋጠም ነው።
Ñ
"ባ"ም የሚወጣው በዚሁ መልኩ ሲሆን ነገር ግን ከ"ሚም" በበለጠ
ግጥሚያው ላይ መጫን ያስፈልጋል።
5) الخيشوم አልኽይሹም፡
ይህ ማለት፦ አፍንጫ ላይ ያለ ቦታ ሲሆን
ነገር ግን ከዚህ ቦታ የሚወጣው ፊደል ሳይሆን የፊደል ባህሪ(ሲፋት) ነው። እርሱም "ጉና" ማለትም "ከአፍንጫ
በኩል የሚወጣ ዜማ "ነው። ይህ ባህሪ የተሰጣቸው ፊደሎች ደግሞ "ኑን እና ሚም" ናቸው። ወላሁ አዕለም።
الترجمة
نفيسة بنت محمد
ትርጉም ነፊሳ ቢንት ሙሃመድ (ኡሙ ዓብደላህ)
مراجعة أستاذ محمد إدريس
እርምት ኡስታዝ ሙሀመድ ኢድሪስ
This comment has been removed by the author.
ReplyDeleteJezakumulah keyr bro. In islam
ReplyDeleteአልሀምዱሊላህ በጣም ስፈልግ የነበረ ትምህርት ነው አላህ ጀዛችሁን በጀነት አል ፊርደውስ ይክፈላችሁ
ReplyDeleteጀዘካላህ ህይርን
ReplyDelete