ተውሒድ አል ኡሉሒያህ
አላህ(ሱብሃነሁ.ወተአላ) የሰው ልጅን እና ከባቢውን የፈጠረው ያለ አንዳች አላማ አይደለም። በል የፈጠረውማ እርሱን በብቸኝነት እንዲገዛው ነው። ለዚህም ነው አላህ በቁርዐኑ እርሱን እንድናመልክ ሲጠራን ማስረጃ የሚያደርገው እኛን መፍጠሩን ነው።
“እናንተ
ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ
በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን
ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ
ይከጀላልና። (እርሱ) ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው፤ ከሰማይም (ከደመና) ውሃን ያወረደ በርሱም ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው፡፡ እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ፡፡” (በቀራህ 21-22)
ይህ አንቀፅ ተውሂዱ ሩቡቢያ ለተውሂዱል ኡሉሂያ ግብዐት መሆኑንና የሰው ልጅ የሚፈለግበት አላህን በአምልኮት ብቸኛ ማድረግ(ተውሂዱል ኡሉሂያ) መሆኑን ያሳያል።
ተውሂዱል-ኡሉሂያ(አላህን በአምልኮት ብቸኛ ማድረግ)
ይህ የተውሂድ ክፍል ተውሂዱል-ዒባዳ በመባልም ይታወቃል። ይህ የተውሂድ
ክፍል አላህ ፍጥረተአለሙን የፈጠረ ነውና አላህን ድካ በደረሰ መተናነስ፣ በመውደድ፣ በመፍራትና ተስፋ በማድረግ በብቸኝነት ሊመለክ
እንደሚገባው ያስተምራል። ነቢያት ሁሉ ይዘው የመጡት መልዕክት ይህ ነበር። ዒባዳን ለአላህን ብቻ ማድረግ!
“ጌታህም (እንዲህ
ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ
ሌላን አትገዙ” (ኢስራዕ-23)
ዒባዳ(አምልኮት) ምንድን ነው?
መልስ፡-ዒባዳ አላህ ለሚወዳቸው ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ንግግሮች እና ተግባሮች ሁሉ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ የአምልኮ ዓይነቶች ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ሰላት፣ ሩኩዕ፣ ሱጁድ ፣ እርድ(ዘብህ) ፣ ኹሹእ(መተናነስ)፣ መመካት፣ዱዓእ፣ፍራቻ (ኸዉፍ)፣ተስፋ ማድረግ (ረጃዕ) ፣ ጠዋፍ እና መሐላ እንዲሁም ሌሎች አላህ የደነገጋቸው የአምልኮ ዘርፎች ሁሉ ዒባዳ ይባላሉ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
(ስግደቴ አምልኮቴም ህይወቴም ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው በል) (አል-አንዓም162)
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በሀዲሰል ቁድስ አላህ እንዲህ እንዳለ ይገልፃሉ
(ባሪያዬ እኔ ግዴታ ያደረግኩበትን ነገሮች ከመፈፀሙ በተሻለ ወደ እኔ የቀረበ የሚያደርገዉ ስራ የለም፡፡) (ቡኻሪ ዘግበዉታል)
የኢባዳ አይነቶች አንዱ ከአላህ ሌላ ከተሰጠ ሽርክ ይሆናል።
A
ከአላህ
ሌላ ማንንም አንለምንም፡፡ አላህ እርሱን ብቻ መለመን እንዳለብን ሲነግረን እንዲህ ይላል፡- (ጌታችሁም አለ! ለምኑኝ እቀበላችሁአለሁና) (አል-ጋፊር
60)
A
·
ከአላህ ሌላ አምልኮታዊ የሆነ ፍራቻን ማንንም ቢሆን አንፈራም፡፡ አላህ እንዲህ ይለናል፡-
(አትፍሯቸውም አማኞች የሆናችሁ እንደሆነ {እኔን ብቻ} ፍሩኝ) (አል-ኢምራን175)
(አትፍሯቸውም አማኞች የሆናችሁ እንደሆነ {እኔን ብቻ} ፍሩኝ) (አል-ኢምራን175)
A
ከአላህ ሌላ በማንም አንመካም፡፡ አላህ አማኞች በእርሱ ላይ ብቻ ሊመኩ
እንደሚገባ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡
(አማኞች እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ) (አል-ማዒዳህ 23)
(አማኞች እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ) (አል-ማዒዳህ 23)
A
ከአላህ
ሌላ ፍጡራን በማይችሉት ጉዳይ ላይ እርዳታን ከአላህ ዉጪ ከማንም አንጠይቅም፡፡ ይህን በማስመልከት አላህ በሱረቱል ፋቲሀ ላይ
ደጋግመን ምናነባቸዉን አንቀፆች አዉርዷል፡፡ (አንተን ብቻ እናመልካለን፤ ከአንተም ብቻ እርዳታ እንጠይቃለን) (አል-ፋቲሀ
5)
A
ከአላህ
ሌላ ከማንም ጥበቃን አንጠይቅም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- “የሰዎች ጌታ በሆነው
እጠበቃለሁ በል” (አል-ናስ
1)
ይህ የተውሂድ ክፍል የአላህ መልዕክተኞች ለሰው ልጆች ለማስተላለፍ
ከአላህ ይዘው የመጡት ዋነኛው መልዕክት ነው፡፡ ሁሉም ነብያቶቸ የዳዕዋቸዉ ዋና ተልዕኮ አምልኮን ባጠቃላይ ለአላህ ብቻ ማድረግ
(ተውሂደል ኡሉሂያህ) ነው፡፡ይህንን አላህ (ሱብሃነሁ.ወተአላ) በቀጣዩ አንቀፅ እንደሚከተለው ይገልፀዋል፡፡
(በየህዝቡም ሁሉ ዉስጥ አላህን አምልኩ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልዕክተኞችን
በእርግጥ ልከናል) (አል ነህል 36)
(ለእያንዳንዳቸው የበለጠ መረጃን የምትሻ ከሆነ ኡሱሉ-ሰላሳን
ተመልከት)
ይህንኑ
የተውሂድ ክፍል እና የነብያቶች መልዕክት ነዉ የፊተኞቹ ሆኑ በዘመናችን የሚገኙ አጋሪዎች ያስተባበሉት፡፡ የመካ ሙሽሪኮች መልዕክተኛው
አንድን አምላክ ብቻ አምልኩ ባሏቸው ጊዜ የሰጡትን ምላሽ በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፡-
(አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸዉን? ይህ አስደናቂ ነገር
ነው‹አሉ›) (ሷድ 5)
አላህ (ሱ.ወ) በየዘመናቱ ከላካቸው ነብያት (ኑህ፣ሁድ፣ሳልህ እና ሹዓይብ) ጥሪ ይህን ይመስል እንደነበር በተለያዩ አንቀፆች ገልፆልናል
(ወገኖቼ
ሆይ! አላህን ተገዙ ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም...) (አል-አእራፍ
59/65/73/85)
No comments:
Post a Comment