ቁርዓንን በምንቀራ ሰዓት በየአንዳንዱ ፊደል አስር አጅር (ምንዳ) እናገኛለን፡፡ ቁርዓንን ማንበብና መሃፈዝ በጣም ከፍተኛ ደረጃ የሚያስገኙ ተግባሮች ናቸው፡፡ ያላቸውን ትሩፋቶች ሁሉ በዚህች አጭር ፅሁፍ መቋጨት አይቻልም፡፡
‹‹እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በምስጢርም ኾነ በግልጽ የለገሱ በፍጹም የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ›› አል-ፋጢር 29
· ከዑመር ኢብኑል ኸጧብ በተወራውና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ (ሠ.ዐ.ወ) ሀዲስ እንዲህ ይላሉ፡-
قَالَ عُمَرُ رَضِىَ اللَّهُ عَنْهُ : أَمَا إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ -صلى الله عليه وسلم- قَدْ قَالَ :« إِنَّ اللَّهَ يَرْفَعُ بِهَذَا الْكِتَابِ أَقْوَامًا وَيَضَعُ بِهِ آخَرِينَ ». رَوَاهُ مُسْلِمٌ
‹‹አላህ በዚህ የአላህ ንግግር(ቁርዓን) ህዝቦችን ከፍ ያደርጋል! ሌሎችንም በዚሁ ቁርዓን ዝቅ ያደርጋል›› ሙስሊም ዘግበዉታል
‹‹ቁርዓንን በአነባበብ ስልቱ ተክኖ የሚያነበዉ እርሱ መልካም እና አላህን ታዛዥ ከሆኑ መልዓክቶች ጋር ነዉ›› ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል
በሌላ ሀዲስ እንዲህ ብለዋል፡-
قال رسول الله صلى الله عليه و سلم : اقرؤوا القرآن فأنه يجيء يوم القيامة شفيعا لأصحابه
(ቁርአንን አንብቡ! ቁርአን በትንሳኤ እለት ለጓደኞቹ አማላጅ
ሆኖ ይመጣል) ሙስሊም ዘግበዉታል
እነዚህና ሌሎች ቁጥራቸዉ በዛ ያሉ ሀዲሶች የቁርአን ህዝቦችን ደረጃ ያሳያሉ
By ustaz sultan khedir
No comments:
Post a Comment