Tuesday, 25 June 2013

በሱና መርከብ እንሳፈር



Ø  በሱና ላይ መጠናከር አዳዲስና መጤ ከሆኑ አመካከቶችና አምልኮዎች እራስን ማላቀቅ ያስልጋል፡፡ በዲን ዉስጥ አዲስ መጤ ነገር ሁለ ቢድዓ ነዉ፡፡ ቢድዓ ግሞ የተወገዘ ነዉ፡፡ መልዕክተኛዉ እንዲህ ብ


‹‹በዚህ በጉዳያችን (በዲናችን) ከእርሱ ያልሆነን ነገር የጠረ (ስራው) ተመላሽ ነው።›› ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡


በሌላ ተመሳሳይ ሀዲስ ፡-

‹‹ትዕዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ (ስራው) ተመላሽ ነው።›› ሙስሊም ከዓኢሻ ዘግበውታል፡፡

Ø  ኢስሊም የተሟላ በመሆኑ ምንም አይነት ጭማሪን አይቀበልም፡፡የተላለፈልንን ሱና ብቻ ብንተገብር ተጠቃሚዎች እንሆናን፡፡ ታላቁ ሰሀቢይ ኢብን መስዑድ አንህ ብ፡-

"ተከተሉ! ቢድዓንም አትፍጠሩ! ሱና በቂያችሁ ነውና!!" ፡፡

ሁዘይፋ ኢብኑል የማን ግሞ እንዲህ ይላል፡-

‹‹የመልዕክተኛው ሰሃቦች ባልሰሩት ማንኛውም የዒባዳ ተግባር አምልኮን አትፅሙ! የመጀመሪያዎቹ መጨረሻዎቹ ምንም የተዉት ነገር የም!›› አቡ ዳዉድና ሌሎች ዘግበውታል፡፡

አንዳን ሰዎች ‹ምንም እንኳ ቢድዓ ቢሆን ጥሩ ስሆነ ቢድአቱል ሀሰናህ ነዉ› ይላሉ፡፡ ዚህ ምላሹ ተከታዩ የዓብደላህ ኢብን  ዑመር ንግግር ነዉ፡፡

‹‹ሁሉም የቢድዓ ተግባር ጥመት ነው! ሰዎች መልካም አድርገው ቢያዩት እነኳ!›› ኢብኑበጣናህና አል-ካኢይና ሌሎችም በትክክኛ ሰነድ ዘግበውታል::

አል-ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፡-

‹‹አንድ ሰዉ፤ በኢስላም ውስጥ አዲስ ነገርን ጥሮ ያ ፈጠራ ጥሩ መስሎ ከታየው ነቢዩ መልእክታቸውን አጓድለዋል ብ ጠርጥሯል፤ ያኔ ዲን ያልነበረ ዛሬ ዲን አይሆንም!›› ፡፡

ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች! ብዙ ሰዎች ሱናን ተግብሮ ሱኒይ መሆንን ከባድ የሚያርገዉ መጤ አመካከቶችና ተግባሮች ልባቸዉን መስጠታቸዉ ነዉ፡፡ እያንዳንዱ ሙስሊም አላህን በመፍራት ሀቅን ሊከተል ይገባዋል፡፡

አቡበከር ኢብኑ-ዒያሽ ‹ሱኒይ ማን ነዉ?› ተብዉ ሲጠየቁ

‹የጠራ መንገድች ሲጠቀሱት ምንም ወገንተኝነት የማያሳይ ነዉ› ኪታብ አሸሪዓ ሊልአጁሪይ ቁጥር 2058

Ø    አል- ኢማም ማሊክ ኢብኑ አነስ እንዱህ ብዋል፡-

‹‹ሱና የኑህ መርከብ ናት! የተሳረባት ይድናል! ወኋላ የቀረ ይሰጥማል!›› ሚፍታሁልጀናህ 46

ሱናን አዉቀን በመተግበር ሁላችንም በኑህ መርከብ እንሳር!!!በሱና መርከብ እንሳፈር


በ ዑስታዝ ጣሃ አህመድ 


No comments:

Post a Comment