ሁለቱ የምስክር ቃሎች የነፃነት ቁልፎች
أشهد أن لا إله إلا الله وأشهد ان محمد رسول الله
"ላኢላሃኢለላህ" ማለት "ካለ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም" ማለት ነው። ይህ ቃል ሁለት ማሰረቶች (አርካን) አሉት።
1)
ነፍይ ᎕ውድቅ ማድረግና
2)
ኢስባት᎕ማፅደቅ ናቸው። ይህም ሲዘረዘር፦
"ላኢላሃ" "አምላክ የለም" የሚለው ቃል ነፍይ ነው።ማለትም አምልኮን በሙሉ ከማንኛውም አካል ወድቅ የሚያደርግ ሲሆን::
"ኢለላህ" "ካለ አላህ በስተቀር" የሚለው ደግሞ "ኢስባት" ነው። ይህም ማለት አምልኮን በሙሉ በእውነት ለአላህ ብቻ ማፅደቅን የሚያስገድድ ቃል ነው።
ስለዚህ ቃልና ትርጉም የሚናገሩ የቁርአን አንቀፆች ስፍር ቁጥር ባይኖራቸውም ለናሙና ያህል ብቻ ሁለት አንቀፆችን እንመልከት።መልካም ቁይታ።
"ኢብራሂምም ለአባቱና ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)።እኔ ከምትገዙት ሁሉ ንፁህ ነኝ።ከዚያ ከፈጠረኝ በስተቀር(አልገዛም) እርሱ በእርግጥ ይመራኛል።" (ዙኽሩፍ 26᎕27)
"እኔ ከምትገዙት ሁሉ ንፁህ ነኝ" የሚለው ይህ "ላኢላሃ" ወይም ነፍይ ነው። ምክንያቱም ኢብራሂም ከባእድ አምልኮዎች ሁሉ ጠርተዋል።ውድቅ አድርገዋቸዋ
"ከዚያ ከፈጠረኝበስተቀር" የሚለው "ኢለላህ" ወይም ኢስባት ነው። እዚህ ጋር ደግሞ በእውነት ተመላኪነትን ለአላህ ብቻ አፅድቀዋልልና።
"በጣኦትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ"
"በጣኦት የሚክድና" ይህ "ላኢላሃ" ነፍይ ነው። ምክንያቱም ጣኦት ማለት ደጋግ የአላህ ባሮች ሲቀሩ ከአላህ ውጪ የሚመለኩ ነገሮች በሙሉ ናቸው።
{በአላህ የሚያምን} ይህ "ኢለላህ" ኢስባት ነው። ምክንያቱም በአላህ የሚያምን ማለት እርሱን በብቸኝነት የሚገዛ ማለት ነውና።
"ሙሃመደን ዓብዱሁ ወረሱሉህ" ማለት "ሙሃመድ የአላህ ባሪያና መልእክተኛ ናቸው" ማለት ነው። ይህም ቃል ሁለት መሰረቶች (አርካን) አሉት።
1)
ጉሉው᎕ድንበር አለማለፍና
2)
ጀፋ᎕ዝቅ አለማድረግ ነቸው። ይህም ሲዘረዘር፦
"ዓብዱሁ" "የአላህ ባሪያናቸው" ሲባል ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሰው ናቸው፡ ሰው ከተወለደበት ተወልደዋል፡ ሰው የሚደርስበት ደርሶባቸዋልና ወዘተ ነገሮችን የሚጠቁም በመሆኑ በእርሳቸው ላይ ድንበር በማለፍ
"ጉሉው" ለአላህ የሚገቡ ነገሮችን ሸርፎና ቆርሶ ለእርሳቸው ከመስጠት ያቅባል። ከዚህ ወስጥ ምሳሌ፦ እርሳቸውን ድረሱልኝ አድኑኝ በአንቱ ሸሸሁና ሌላም ሌላም ይገኝበታል።
"ወረሱሉሁ" የአላህ መልእክተኛ ናቸው" ሲባል ደግሞ አላህ ከፉጡሮቹ የበላይ አድርጎ መልእክቱን እንዲያደርሱ የመረጣቸው በመሆኑ እንደተራ ሰው ታይተው "ጀፋ" ዝቅ እንዳይደረጉ ያቅባል። ከዚህ ውስጥ ምሳሌ፦በሱናቸው አለመስራት ይገኝበታል። ምክንያቱም አንድ ሰው የሚወደውን የሚያልቀውን የሚያከብረውን አካል ታላላቅ በሆኑ የህይወት ጉዞዎቹ አይደለም ጥቃቅን በሚባሉት እንኳ ይከተለዋል። እርሱን ሆኖ መገኘት ቢሳነው እንኳ እርሱን መስሎ ለመቅረት ይጥራል፡ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው እነዚህን ታላቅ የምስክር ቃሎች የሚተነትኑ አንቀፆች በርካታ ቢሆኑም የተጠቀሰውን መሰረት የሚገልፅ አንድ ብቻ እንጥቀስ፦
"እኔ አምላካቹህ አንድ አምላክ ብቻ ነው የሚል ወደ እኔ የሚወረድልኝ ቢቴያችሁ ሰው ብቻ ነኝ" (አል ከ ህፍ 110)
{አንድ አምላክ ብቻ ነው የሚል ወደ እኔ የሚወርድልኝ} ይህ "ጀፋ" ዝቅ እንዳይደረጉ ያቅባል። ምክንያቱም ወህይ የሚወርድላቸው የአላህ መልእክተኛ ናቸውና፡
{ቢጤያችሁ ሰው ነኝ} ይህ ደግሞ "ጉሉው" ድንበር እንዳይታለፍባቸው ያቅባል። ምክንያቱም እንደኛው ሰው ናቸውና። አበቃሁ።
እናንተ የተከበራችሁ እህት ወንድሞቼ እንግዲህ በዚህ መልኩ ቁርአንን እያስተነተንን ጥልቅ ሚስጥሩን እምቅ ሃብቱን በመቋደስ ለህይወታችን ፈውስና ብርሃን ልናገኝላት ይገባል። በተለይ ደግሞ የእርሱው ወር የሆነው
ታላቁ እንግዳ መጣሁ መጣሁ እያለን ነው። አላህ ሁላችንንም በሰላም ያድርሰን። እስኪ ሽልማት የሌለው አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ። ከላይ የተብራሩትን የምስክር ቃሎች የሚገልፁ ሁለት አንቀፆችን ለእያንዳንዱ አንዳንድ ማለት ነው አቅርቡልኝ።
No comments:
Post a Comment