"ትእግስት"
የአማኞች መሪ ዓልይ (ረዲየላሁ ዓንሁ) ስለ "ትእግስት" ሲናገር እንዲህ ብሏል፦
"ኢማን በአካል ቢመሰል ኖሮ ትእግስት እራሱ (አናቱ) ይሆን ነበር።"
አዎ ትእግስት ታላቅ ጌጥ ነው አማኞች ሚጊያጊያጡበትና ሚሸላለሙበት።እርሱ ማለት ያ አላህ ( ሱብሃነሁ ወተዓላ) የፉጡሮች ቁንጮ የሆኑትን መልእክተኞቹን ያዘዘበት
{ከመልእክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የሆኑት እንደታገሱ ታገስ}
ይህች ምድር የፈተናና የትግል ሜዳ በመሆኗ ለአማኞች የትእግስትን ኩታ መደረብ ግድ ሆነባቸው።
@ እውቀት ትእግስት ይፈልጋል። እንቅልፍን መዝናናት መደሰትን ሌላም ሌላም ነገሮችን ትቶ አሊያ ለእነርሱ ከሚውሉ ጊዚያቶች ሽርፎና ቆርሶ እውቀት ሲገበይ፡ ይህንንም ግብይት ሲጠና ወዘተ ትእግስት ይፈልጋል።
@ ተግባርም ትእግስት ይፈልጋል። ሰው ሲያሻርክ አንተ ግን አላህን በኢኽላስ ስትገዛ፡ ሰው ስፍር ቁጥር የለሽ ኢማሞችን ለህይወት ጉዞው ሲያበጅ አንተ ግን መሪዬና አርአያዬ ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ብቻና ብቻ ናቸው ስትል እና ወዘተ ትእግስት ይፈልጋል።
@ ዳዕዋም ትእግስት ይፈልጋል። አማኝ እህትና ወንድሞች አለፍም ሲል ባጠቃላይ የሰው ልጆች አንተ የተቋደስከውን የተውሂድ ብርሃን እንዲጋሩህ ስትጠራቸው ስታመላክታቸው ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ለይሆን ይመቻልና ዳጎስ ያለ ትእግስት ይጠይቃል።
በእነዚህ ነገሮች ላይም የሚጋረጡን ነገሮች ለማለፍ እንዲሁ ትእግስት ይፈልጋል።
አላህ ሁላችንንም ታግሰው ምንዳቸውንም ያለ ግምት ከሚሰጡት ያድርገን።
No comments:
Post a Comment