Wednesday, 12 March 2014

ከዛፍ ከድንጋይና ከመሳሰሉ ነገሮች በረከትን መፈለግ

ከዛፍ ከድንጋይና ከመሳሰሉ ነገሮች በረከትን መፈለግ
 በረከትን መፈለግ ሸሪዓው ከፈቀደው እና ካልፈቀደነው ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ሸሪዓው ከሚፈቅዳቸው ነገሮች ለምሳሌ ከቁርዓን በመካ በመዲናና በበይተል መቅዲስ ከመስገድ በረከት ለማብዛት መጣር የተወደደ ተግባር ሲሆን ሸሪዓው ከማይፈቅዳቸው ነገሮች ግን ለምሳሌ ከዛፍ ከድንጋይና ከቀብር በረከትን መፈለግ ሽርክ ነው፡፡ አቡ ዋቂድ አልለይሢይ እንዲህ ብለዋል፡-                                                          “አዲስ ሰለምቴዎች ሳለን ከነብዩ ጋር ወደ ሁነይን ስንሄድ አጋሪዎች እርሱ ዘንድ በመቀመጥና መሳሪያቸውን ላዩ በማንጠልጠል በረከትን የሚፈልጉበት ዛፍ ነበራቸውና በአንዲት ዛፍ ስናልፍ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ እነሱ የሚያንጠለጥሉባት ዛፍ እንዳለቻቸው ሁሉ ለኛም ማንጠልጠያ ዛፍ አድርጉልንአልናቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛም በቁጣ እንዲህ አሉአላሁ አክበር! ይህ የተለመደ መንገድ ነው ነፍሴ በእጁ ባለችው እምላለሁ የኢስራኤል ልጆች ለሙሳ እንዲህ ያሉትን አይነት ነው ያላችሁት፡-
ለነርሱ አማልክት እንዳሏቸው ለኛም አምላክን አድርግልን አሉት፤ እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ አላቸው” (አል አዕራፍ)
"ከበስተፊታችሁ የነበረን መንገድ ትከተላላችሁ”                                                       በዚህ ሀዲስ ከዛፍ በረከትን የፈለጉትን ሰዎች ሌላ አምላክ ከፈለጉ ሰዎች ጋር ማመሳሰላቸው የሚያመለክተው ከእንደዚህ አይነት ነገሮች በረከትን መፈለግ ማጋራት እንደሆነ ነው::
አንባር ክርና የመሳሰሉ ነገሮችን ማጥለቅ
ዓረቦች ከእስልምና በፊት በነበረው የድንቁርና ዘመን ይህንንና የመሳሰሉትን ክፋትን ለመመከት፣ መልካምን ለማስገኘት ወይም ከቡዳ ለመጠበቅ ያደርጉት ነበር፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
«ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን (ጣዖታት) አያችሁን? (ንገሩኝ) አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነርሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈቅደኝ እነርሱ ችሮታውን አጋጆች ናቸውንበላቸው፡፡ «አላህ በቂዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ» በል፡፡ (አል ዙምር 38)
በሌላም አንቀጽ እንዲህ ይላል፦«እነዚያን ከእርሱ ሌላ (አማልክት) የምትሏቸውን ጥሩ፡፡ ከእናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን (ወደ ሌላ) ማዞርንም አይችሉም» በላቸው፡፡ (አል ኢስራህ 56)
ከዒምራን ኢብኑ ሁሰይን እንደተዘገበው ‹‹ነብዩ አንድ ሰውዬ እጁ ላይ ከመዳብ የሆነ አንባር አጥልቆ ሲያዩትይህ ምንድነው?” ብለው ጠየቁትለድካም በሽታ ነውአላቸው:: እሳቸውም እንዲህ በማለት ወቀሱትአውልቃት ድካምን እንጂ አትጨምርልህም እጅህ ላይ እያለች ከሞትክ አትድንም፡፡››
ከሁዘይፋ ኢብኑል የማን እንደተዘገበው                                               ‹‹አንድን ሰው በመታመሙ እጁ ላይ ክር አስሮ አየውና ከበጠሱበት በኋላ ይህን አንቀጽ አነበቡ፦
وَمَا يُؤْمِنُ أَكْثَرُهُم بِاللَّهِ إِلَّا وَهُم مُّشْرِكُونَ
‹‹አብዛኞቻቸውም፤ እነሱ አጋሪዎች ኾነው እንጂ በአላህ አያምኑም፡፡›› (ዩሱፍ 16)
አንባር፣

ክርና የመሳሰሉትን ማጥለቅ ሸሪዓዊ ድንጋጌው ሀራም (ክልክል) ሲሆን የተጠለቀው ራሱ ያለ አላህ ፈቃድ ተፅእኖ ያሳድራል የሚል እምነት ካለው ከአላህ ውጭ አስተናባሪ ጌታ አለ ማለት በመሆኑ በአላህ ጌትነት ላይ ትልቁን ሽርክ አጋርቷል ማለት ነው::                                                       ነገሮች ሁሉ በአላህ እጅ እንደሆኑና ያጠለቀው ነገር ግን ለፈውስ ምክንያት ብቻ እንደሆነ ቢያምን ደግሞ ትንሹን ሽርክ ፈፅሟል፡፡ ምክንያቱም ሰበብ ያልሆነን ነገር እንደሰበብ ቆጥሮ በልቡና በስራውም ከአላህ ሌላ ወደሆነ አካል ዞሯል፡፡ ይህ ደግሞ ወደ ትልቁ ሽርክ ለመሸጋገር በር የሚከፍት ነው፡፡

No comments:

Post a Comment