Wednesday, 12 March 2014

እርዝ

እርዝ 
. ትርጉሙ፦
 እርዝ ከክፋት ይጠብቅ ዘንድ ታሽጎ አንገት ላይ የሚንጠለጠል ፅሁፍ፣ ክሮች፣ አጥንቶች የመሳሰሉ ነገሮች ሲሆን ድሮ ዓረቦች በተሳሳተ አመለካከታቸው ልጆችን ከሰው አይን ለመከላከል የሚያንጠለጥሉላቸው ጥቅምን ለማግኘት ወይም ጉዳትን ለመከላከል በማሰብ የሚደረግ ነው፡፡
. ሸሪዓዊ ብይኑ፦
 ሀራም (የተከለከለ) ከመሆኑም በላይ ከሽርክ አይነቶች አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱ ከአላህ ውጭ በሆነ ነገር መንጠልጠል ነው፡፡ ክፉን መካች አላህ ብቻ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ጎጂን ነገር መከላከል ያለበት በአላህ በስሞቹና በባህሪያቱ ብቻ ነው፡፡                                                                =>ኢብኑ መስዑድ እንዳሉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው                                                 ‹‹ሩቃ፣ እርዝና መስተፋቅር መስራት ሽርክ ነው”                                                           =>አብደላህ ኢብኑ ዑከይም እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል                                “በአንድ ነገር ላይ የተንጠለጠለ ወደ ለርሱ ይተዋል”                                                   =>ዑቅበት ኢብን ዓሚር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል                                   “እርዝን ያንጠለጠለ አላህ አይሙላለት፣ ዛጎልንም ያንጠለጠለ አላህ አይተውለት”                                  =>ዑቅበት ኢብን ዓሚር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል                       እርዝን ያንጠለጠለ ሽርክን ፈፅሟል                                                              እነዚህና መሰል ጥቅሶች ዓረቦች በብዛት ሲያንጠለጥሉት የነበሩትን ሽርካዊ እርዞች የሚከለክሉ ሲሆኑ የተከለከሉትም ከአላህ ውጭ በሆነ ፍጡር ላይ መንጠልጠል በመሆኑ ነው፡፡
. የሚንጠላጠለው ፅሑፍ የቁርአን ቃል ከሆነ፦
 ዑለማዎች በዚህ ዙሪያ አልተስማሙም ከፊሉ የሚፈቅድ ሲሆን ሌላው ደግሞ ይከለክላል፡፡ ቁርአንን ለፈውስ ማንጠልጠል አይቻልም የሚሉ አቋሟቸው ከአራት ምክንያቶች አንፃር ሲታይ ትክክል ነው፡፡              
1. ነብዩ እርዝን የከለከሉት በጥቅሉ ሲሆን ይህን አይነቱን ነጥሎ የሚያወጣ ማስረጃ አለመኖሩ፡፡        2. ይህን መፍቀድ ከቁርአን ያልሆነን ፅሁፍ ለማንጠልጠል መንገድ ስለሚከፍትና ወደ መጥፎ የሚመራን መንገድ መዝጋት ደግሞ ተፈላጊ ስለሆነ::                                               3. አንጠልጣዩ በመፀዳጃ፣ በኢስቲንጃና በመሳሰሉት ቦታ ይዞት ስለሚገኝ ቁርአንን ዝቅ የሚያደርግ በመሆኑ፡፡                                                                            4. በቁርአን መፈወስ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት ስለተገለፀ (እሱም ህመምተኛው ላይ መቅራት ነው) እና ይህን መተላለፍ ስለማይቻል፡፡
ሩቃ
. ትርጉሙ፦
 “ሩቃሩቅያ ለተሰኘው የዓረብኛ ነጠላ ቃል ብዜት ሲሆን ሩቅያ ማለት በሽተኛን ለመፈወስ የሚነበነቡ ከቁርአንም ይሁን ከሀዲስ ጥቅሶች ማለት ነው፡፡
. ሸሪዓዊ ብይኑ፦
 የተፈቀደ ነው፡፡ ከማስረጃዎች ውስጥ ዓውፍ ኢብኑ ማሊክ እንዳሉትበድንቁርና ዘመን በሽተኛ ላይ እናነብ ነበርና የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እንዴት ያዩታል? ብለን ጠየቅናቸው፡፡ እሳቸውም ምታነቡትን ግለፁልኝ፤ ማጋራት የሌለበት እስከሆነ ድረስ በሽተኛ ላይ ማንበብ ችግር የለውም አሉ”                                 =>አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ብለዋል                                                              “የአላህ መልዕክተኛ ለቡዳ በሽታ፣ ለመነደፍና ቁስለት ሩቃ ማድረግ ፈቅደዋል”                                  =>ጃቢር ኢብኑ ዐበደላህ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል                                    “ወንድሙን (ከህመሙ ለመፈወስ በመቅራት) መጥቀም የቻለ ያድርግ››                                      =>ከአዒሻ እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ ከኛ ውሰጥ አንዱ ሲታመም በቀኝ እጃቸው እየዳበሱት እንዲህ ይሉ ነበር:-                                                                                                  “የሰዎች ጌታ ሆይ! ጉዳትን አስወግድ፤ፈውሰው አንተ ፈዋሸ ነህ ከአንተ ሌላ ፈዋሽ የለም ህመምን በማያስቀር ፈውስ ፈውሰው
. መስፈርቶቹ፦
 ሩቃ የሚፈቀደው ሶስት መስፈርቶች ሲሟሉ ነው:: እነሱም፡-
 አንደኛ፡- ከአላህ ፈቃድ ውጭ ያድናል በሚል ሊታመን አይገባም፡፡ ከአላህ ፈቃድ ውጭ እንደሚጠቅም ማመን ሽርክ በመሆኑ የተከለከለ ነው፡፡
 ሁለተኛ፡- ሸሪዓን የሚጋጭ መሆን የለበትም፡፡ ለምሳሌ ከአላህ ሌላ መለመን ወይም ከጭንቅ እንዲገላግል ጋኔንን መጥራት የመሳሰሉት ከታከሉበት ሽርክ በመሆኑ ክልክል ይሆናል፡፡
 ሶስተኛ፡- ግልፅ የሆነ ትርጉም ያለው መሆን አለበት፡፡ ትርጉም የሌለው አተታ ከሆነ አይፈቀድም፡፡
ኢማም ማሊክ እንዲህ በሚል ተጠየቁየታመመ ሰው ላይ መቅራት ይቻላልን? እሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱበመልካም ቃላቶች ከሆነ ችግር የለውም፡፡

. ክልክል የሆነ ሩቅያ፡-

 ከላይ የተጠቀሱ መሰፈርቶች ያልተሟሉበት ሩቅያ በመሉ ክልክል ነው:: ለምሳሌ አንባቢው ወይም የሚነበብለት ሰው ሩቅያ ራሱን ችሎ ፈውስ ነው በሚል የሚያምን ከሆነ ወይም ሩቅያው የሽርክ የቢድዓ የመሳሰሉ ቃላቶችን ያቀፈ ከሆነ ወይም ደግሞ ትርጉም በሌለው አተታ ከሆነ አይፈቀድም፡፡

No comments:

Post a Comment