Thursday, 20 March 2014

ኩፍር (ክህደት)

ኩፍር (ክህደት)
. ትርጉሙ፡-                                                                              ኩፍር በዓረብኛ ቋንቋ ትርጉሙ መሸፈን ወይም መደበቅ ማለት ነው፡፡
ሸሪዓዊ ትርጉሙ፡-                                                                                  የእምነት ተቃራኒ ማለት ነው፡፡ ማስተባበል አብሮት ኖረም አልኖረም በአላህና በመልዕክተኛው አለማመን ብቻ ኩፍር (ክህደት) ይባላል፡፡ እንዲያውም ጥርጣሬ ወይም እያወቀ ከምቀኝነት፣ ከኩራትና ስሜትን ከመከተል የመነጨ እምቢተኝነት ኩፍር (ክህደት) ይባላል፡፡
. የኩፍር (የክህደት) አይነቶች                                                                ኩፍር ሁለት አይነት ነው ትልቁ ኩፍርና ትንሹ ኩፍር
 ትልቁ ኩፍር ጀሀነም ውስጥ መዘውተርን የሚያስከትል ሲሆን ትንሹ ኩፍር ግን መዘውተርን ባያስከትልም ከባድ ዛቻ እንዲገባው ያደርጋል::
አንደኛ፡ ትልቁ ኩፍር
 ትልቁ ኩፍር አምስት አይነት ነው፡-
 1. ማስተባበል፡- መልዕክተኞች ውሸታሞች እንደሆኑ ውሰጣዊም ይሁን ውጫዊ መልክታቸው ሀሰት እንደሆነ ማመን ማለት ነው፡፡          ለዚህ ማስረጃ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹በአላህ ላይም ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ወይም እውነቱ በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ ይበልጥ በዳይ ማነው? በገሀነም ውስጥ ለከሓዲዎች መኖሪያ የለምን?››(አል ዓንከቡት 68)
2. በኩራት ያለመቀበል ኩፍር፡- ይህ ማለት መልዕክተኛው እውነተኛና እውነትን ይዞ የመጣ መመሆኑን ቢያምንም ነገር ግን በትእቢትና በኩት ለርሱ ፍርድና ትዕዛዝ እጅ አለመስጠት ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ፤ ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ብቻ ሲቀር እምቢ አለ፤ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ፡፡›› (አል በቀራህ 34)
3. የጥርጣሬ ኩፍር፡- ማመንታትና መልዕክተኞች እውነተኛ ስለመሆናቸው እርግጠኛ አለመሆን ማለት ነው፡፡  ለዚህም ማስረጃ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹እርሱም ነፍሱን በዳይ ኾኖ ወደ አትክልቱ ገባ፡፡ «ይህች ዘለዓለም ትጠፋለች ብዬ አልጠረጥርም» አለ፡፡ ሰዓቲቱንም ቋሚ (ኋኝ) ናት ብዬ አልጠረጥርም፡፡ (እንደምትለው) ወደ ጌታዬም ብመለስ ከእርሷ የበለጠን መመለሻ በእርግጥ አገኛለሁ» (አለው)፡፡ ጓደኛው (አማኙ) እርሱ ለእርሱ የሚመላለሰው ሲኾን «በዚያ ከዐፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከፈጠረህ፣ ከዚያም ሰው ባደረገህ (አምላክ) ካድክንአለው፡፡ እኔ ግን እርሱ አላህ ጌታዬ ነው፤ (እላለሁ)፡፡ በጌታዬም አንድንም አላጋራም፡፡››                       (አል ከህፍ 35-38)
 4. የቸልተኝነት ኩፍር፡- መሉ በሙሉ በጆሮው፣ በልቡም፣ ሆነ በስራው መልዕክተኛው ካመጡት መልዕክት ቸል ብሎ መተው ማለት ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃ አላህ አንዲህ ብሏል፡-
‹‹እነዚያ የካዱትም ከተስፈራሩት ነገር (ትተው) ዘዋሪዎች ናቸው፡፡››(አል አህቃፍ 3)
 5. የንፍቅና ኩፍር፡- እምነትን ከላይ በማንፀባረቅ ክህደትን በውስጥ በመደበቅ የልብ ንፍቅና፡፡                                                             ለዚህም ማስረጃ አላህ እንዲህ ብሏል -
‹‹ይህ እነርሱ (በምላስ) ያመኑ ከዚያም (በልብ) የካዱ በመኾናቸው ነው፡፡ በልቦቻቸውም ላይ ታተመባቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም፡፡››  (ሙናፊቁን 3)
ኒፋቅ ሁለት አይነት ነው፡-
 1. የልብ ንፍቅና፡- ይህ ከእስልምና የሚያስወጣ ሲሆን ስድስት አይነት ነው፡፡                            መልዕክተኛን ማስተባበል፣ መልዕክተኛው ካመጣው ውስጥ የተወሰነውን ማስተባበል፣ መልዕክተኛውን መጥላት፣ የመልዕክተኛው ሀይማኖት ሲዋረድ መደሰትና የመልዕክተኛው ሃይማኖት የበላይ ሲሆን መጥላት ናቸው፡፡                                                                       2. የተግባር ንፍቅና፡- ይህ ትንሹ ኩፍር በመሆኑ ከእስልምና ባያስወጣም ነገር ግን አደገኛ ወንጀልና ከባድ ኃጢአት ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ነብዩ (..) በሀዲስ እንዲህ በማለት የጠቀሱት ይካተታሉ ‹‹አራት ባህሪዎች ያሉበት ሙልጭ ያለ መናፍቅ ይሆናል ከአራቱ አንዱ ያለበት ሰው ግን እስኪተወው ድረስ ከመናፍቅ ባህሪዎች አንዱ አለበት ሲታመን በካድ፣ ሲናገር መዋሸት፣ ቃሉን የሚያፈርስና ሲከራከር ድንበር መጣስ፡፡›› ቡኻሪና ሙስሊም በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል ‹                                                ‹የመናፍቅ ምልክት ሶስት ነው ሲናገር መዋሸት፣ ቀጠሮን ማፍረስና ሲታመን መካድ፡፡››
ሁለተኛ፡ ትንሹ ኩፍር
 ትንሹ ፈፃሚውን ከእስልምና አያስወጣውም ጀሐነም ውስጥ እንዲዘወትርም አያደርግም ነገር ግን ከባድ ዛቻም ይጠብቀዋል፡፡                                                             ትንሹ ኩፍር ውለታን መካድና እንዲሁም በቁርአንና በሀዲስ ጥቅሶች ኩፍር በመባል ተሰይሞ ነገር ገን የትልቁን ኩፍር መጠን ያልደረሰ ነው፡፡ የሚከተለው የአላህ ቃል ለዚህ ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡-
‹‹አላህ ጸጥተኛ፣ የረካች፣ ሲሳይዋ ሰፊ ኾኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢኣት የረኃብንና የፍርሃትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ (መካን) ምሳሌ አደረገ፡፡›› (ነህል 112)
የነብዩም (ሠለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦                                                              ‹‹ሁለት ነገሮች ኩፍር ናቸው ዘርን ማንቋሸሽና በሞተ ሰው መጮኽ››                                           ‹‹ከእኔ በኋላ ወደ ኋላ በማፈግፈግ ኩፋሮች ሆናችሁ አንዱ የሌላውን አንገት እንዳይቀላ››
 እነዚህና የመሳሰሉት ከትልቁ ያነሱ ኩፍሮች ሲሆኑ ከእስልምና የማያስወጡ ናቸው:: አላህ እንዲህ ብሏል
‹‹ከምዕምናንም የኾኑ ሁለት ጭፍሮች ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ፡፡ ከሁለቱ አንደኛይቱም በሌላይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ አላህ ትዕዛዝ እስከምትመለስ ድረስ ተጋደሉ፡፡ ብትመለስም በመካከላቸው በትክክል አስታርቁ፡፡ በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና፡፡ ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡›› (አል ሁጅራት 9-1)                                                                                              መገዳደላቸው እንዳለ ሆኖ አላህ አማኞች ብሎ ሰየማቸው፡፡  ሌላው ማስረጃ፡-
‹‹አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ፡፡›› (አል ኒሳእ 48)
ይህ የተከበረ አንቀጽ እንደሚጠቁመው ከሽርክ በታች ያለ ማንኛውም ወንጀል በአላህ ፍላጐት ስር መሆኑን ነው፡፡ ማለትም ከፈለገ በኃጢአቱ መጠን ይቀጣዋል ከፈለገ ደግሞ ከመጀመሪያው ይቅር ይለዋል፡፡ ሽርክ የፈፀመ ግን አንቀፁ ላይ በግልፅ እንደተነገረው አላህ አይምረውም፡፡                               አላህ እንዲህ ብሏል፦
إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

‹‹እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡›› (አል ማኢዳህ 72)

No comments:

Post a Comment