ሃላፊነት
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡትና ኢብኑ ዑመር ባወራው ሃዲስ ላይ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ
ወሰለም)
" ሁላችሁም ጠባቂዎች (እረኞች) ናችሁ የጠበቃችሁትንም ነገር ተጠያቂዎች ናችሁ። መሪ በህዝቦቹ ላይ ጠባቂ ነው።ከጠበቀውም ነገር ተጠያቂ ነው። ወንድ የቤተሰቦቹ ጠባቂ ነው። ከጠበቀውም ነገር ተጠያቂ ነው። ሴት በባሏ ቤት ጠባቂ ነች።ከጠበቀችውም ነገር ተጠያቂ ነች። ሰራተኛ በአለቃው ንብረት ላይ ጠባቂ ነው። ከጠበቀውም ነገር ተጠያቂ ነው። አዎ ሁላችሁም ጠባቂዎች ናችሁ ከጠበቃችሁትም ነገር ትጠየቃላችሁ። "
ሱብሃነ ረቢ፡ ምንኛ ታላቅና ያማረ ንግግር ነው። ሁሉም ይህንን ሃዲስ በወጉ በመገንዘብ ሃላፊነቱን ይወጣ።
1) አንተ መሪ ሆይ አንባ ገነንነቱንና መጨቆኑን ትተህ ህዝቦችህን በፍትህ ምራ።
2)
አንተም ወንድም ሆይ ቤተሰቦችህን ኢስላም ባስቀመጠው መልኩ አስተዳድራቸው። ነገ ባንተ ስር ኖረው አላህን የማያውቁ፡ ሰላት የማይሰግዱ ሌላም ሌላም አይነት ቤተሰቦችህ ትጠየቅባቸዋለህ። አላመላከትካቸውምና። ጠንቀቅ በል።
3)
አንቺም እህት ሆይ ባልሽን በአላህ አምልኮ (ዒባዳ) ላይ አጋዥ ሁኚ። "ጨቅጫቃ ሚስት ያለው ለቅሶ ቤት አይሄድም" እንዲሉ ሲወጣ ሲገባ ይህ አለቀ ይህ ደቀቀ በማለት ከዒባዳው ከዳዕዋው አታርቂው። ልጆችሽን የ "ቁርአንና ሱና" ትውልዶች ለማድረግ ጥረትሽ ሁሉ ሊፈስለት ይገባል። የዚህ ተቃራኒ ከሆነ ግን ውጤቱ የከፋ ነው።
4)
አንተ ሰራተኛ ሆይ በተመደብክበት በእያንዳንዱ የስራ መስክ ኢስላም እንዳዘዘህ በጥራትና በታማኝነት መወጣት አለብህ። አዎ ይህ ከሆነ፦አንተ ከሚዋሹትም፡ ከሚሰርቁትም፡ ሰአታቸውን ከሚያሳልፉትም ወዘተ ውስጥ አትሆንም።
በእውነቱ ይህ የተከበረ "ሃዲስ" ሁሉም በያዘውና ጠባቂ በተደረገበት ነገር ላይ ሃላፊነቱን "ኢስላም" ባስቀመጠው መልኩ እንዲወጣ የሚያሳስበው ነው። ይህን ካላደረጉ ግን መልስ በሌለው ተጠያቂነት መፋጠጡ የካፋና የበረታ ነው ሚሆነው። በእውነቱ የብእር ደሃ መሆን ሆነና ነው እንጂ፦ ሃብታሞቹ ከዚህ ተአምራዊ ንግግር ብዙ ሚስጥሮችን ፈልቅቀው ማውጣት ይችላሉ።

አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ሁላችንንም የተጣለብንን ሃላፊነት እርሱን በሚያስደስተው መልኩ ምንወጣው ያድርገን። አሚን።

No comments:
Post a Comment