Wednesday, 12 March 2014

ዕውቀት

ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ምስጋና ይገባው። የአላህ ውዳሴና ሰላም በነብያቶች መደምደሚያ ነቢዩ (ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በጓዶቻቸውና ቀናውን ጎዳና በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን።                                                   አስታውስ! አላህ ይዘንልህና። አላህ ከጃሂሊያ አውጥቶ ለኢስላም እንዳበቃን፤ ከዚያ ፈጣሪ ተዘንግቶ ጣኦታት ከሚመለኩበት፣ ሰብዐዊነት ጠፍቶ ጭካኔ ከሰፈነበት፣ ሴት ልጅ ከነህይወቷ ከምትቀበርበት ዘመን አላህ በቃችሁ ሲለን ወደ ብርሃን አወጣን። ታላቁን ነቢይ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ተጣሪ አድርጎ ላከልን። ከሀይማኖትም ኢስላምን መረጦ በርሱም ላይ እንድንሞት አዘዘን።
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَجِيبُوا لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمْ لِمَا يُحْيِيكُمْ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልክተኛው) ሕያው ወደ ሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልክተኛው ታዘዙ፡፡አንፋል-24
እስቲ ላፍታ ቆም በልና ያንተንና የሙስሊሞችን ሁኔታ ተመልከት፤ ነቢዩ ነቢዩ (ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እና ሶሀቦች ከነበሩበት ዘመን ጋር አስተያየው። በርግጥ በነሱ መንገድ ላይ ነን? ካስተዋልክ ሁኔታው የተገላቢጦሽ ሁኖ ታገኘዋለህ። ብዙዎች ላይ ከልክ ያለፈ አላዋቂነት ተንሰራፍቶ፣ ዝንጉነትና ስንፍና በዝቷል። ሙስሊሞች ከየአቅጣጫው በተለያዩ ፈተናዎች ተወጥረው ሲዋልሉ ታያለህ። ፈተና እንደማይቀርልን ተነግሮን ሳለ ብዙዎች ግን ሲወድቁ ትታዘባለህ።
أَحَسِبَ النَّاسُ أَن يُتْرَكُوا أَن يَقُولُوا آمَنَّا وَهُمْ لَا يُفْتَنُونَ
ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን?” (69-2)
ታዘብ! ዛሬ አፈንጋጮች በዝተዋል፤ ሰዎችም ከነቢዩ ነቢዩ(ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይልቅ ግለሰቦችን በጭፍን መከተልን ተያይዘዋል። ሱናን ትተው ቢድዐ ውስጥ ተዘፍቀዋል። በመሰረተቢስ እምነቶች ተተብትበው ዳግም ወደ ሽርክ ነጉደዋል። ባዕድ አምልኮ በከፊል አንጃዎች ውስጥ ነፍስ ዘርቷል ብሎም ተንሰራፍቷል። ይሄኔ የሙስሊሞች አንድነት ተንዶ በካፊሮችና ጠላቶቻቸው መጫወቻ ሁነዋል። በጉልበትም በባህልም ተወረዋል። ማንነታቸውን ዘንግተው ለዲናቸው ባይተዋር ሁነዋል። ወደ ሱና የተጠጋ፣ተውሂድ ላይ የቆመም እንደ እንግዳ ታይቷል። ነቢዩ(..) እንዲህ ብለው ነበር- ኢስላም እንግዳ ሆኖ ነው የጀመረው ወደፊትም እንግዳ ሁኖ ይመለሳል፤ እንደ እንግዳ ለሚታዩት ጡባ(ጀነት) አለችላቸውአልባኒ ሰሂህ ነው ብለዋል                                                                 ዛሬ ብዙዎች የተፈጠሩበትን አላማ ረስተዋል፣ አኼራንም ዘንግተዋል። አላህን መታዘዝ ኋላ ቀርነት መስሏቸው በማመጽ ስልጣኔ ተኮፍሰዋል። ማሀይምነት ወርሷቸው ኋሊዮሽ ተጉዘዋል። የጀነት ትኬት እንደደረሰው ዒባዳን ትተዋል። ገሩን ዲን አክብደው ከባዱን ወንጀል አቅለዋል። ውድ ወንድሜ/እህቴ! እስቲ መለስ እንበልና ራሳችንን እንገምግመው። ንቁ!!! ካለንበት ፈተና የምንወጣው ወደ ቁርዐንና ሀዲስ ስንመለስ ብቻ ነው። ዳግም ወደ አላህ ፊታችንን ስናዞር፤ በትዛዙም ስንቆም ነው። አዎን! የናቅነውን ሱና መልሰን አንስተን መታወቂያችን ስናደርግ፣ የነዛን ብርቅዬ ሰለፎች(ቀደምቶች) አካሄድ ስንይዝ፣ በእምነታችን ቀጥ ስንል ነው፤ ያቺን ተናፋቂ ጀነት የምናገኘው።
እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡ (41-20)
ወደ ዲናችን መመለስ ለዱኒያም ለአኸይራም ስኬት ቁልፍ ነው። ይህን ቁልፍ ማግኘት ደግሞ በሁላችንም ላይ ግድ ነው አንተንም ጨምሮ። የዚህ ቁልፍ ማግኛው መንገድ ደግሞ እውቀት ብቻ ነው፤ ሸሪዐዊ ዒልም!!! ታዲያ ምን ትጠብቃለህ?
ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡” (ነህል-97)
ኢማሙል ቡኻሪ በሐዲስ ስብስባቸው ውስጥእውቀት ከንግግርም ከስራም ይቀድማልሲሉ ርዕስ አስቀምጠዋል። ሀፊዝ ኢብኑሀጀር በዚህ አባባል የተፈለገበት ይላሉ፡- “እውቀት ለንግግርና ለስራ ትክክለኝነት መስፈርት መሆኑ ነው።…” ፈትሁል ባሪ                                                                                                            አዩሀል ሙስሊሙን! ከንግርህም ሆነ ከስራህ በፊት እውቀት ይቀደማልና ዒልምን ተዋወቀው። ከአንተ የሚጠበቀውን ትተገብር ዘንድ ለእውቀት የጎላ ስፍራን ለግስ። አላህ ጀነትን ያዘጋጀው ለሚታዘዙት ባሮቹ ነውና እርሱን ትታዘዝ ዘንድ ትእዛዛቱን ተማር። አላህ ምህረቱን ያዘጋጀው ከከለከላቸው ለሚታቀቡት አማኞች ነውና የከለከለህን በሙሉ ትርቅ ዘንድ ወደ ሸሪዐዊ እውቀት ፍጠን። ወደ ቁርዐንና ሐዲስ ተጣደፍ። ቀናውን ጎዳና ልትይዝ ይከጀላልና።
እኔ ሁለት ነገሮችን ትቼላችሁዋለሁ፣ እነሱን እስከያዛችሁ አትጠሙም የአላህ ኪታብ እና የኔ ሱና ናቸው                           ነቢዩ  (ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
አንተ/ በርግጥ አሁን እውቀትን በመገብየት ላይ ነህን? ወይስ ተዘናግተሀል?... አአ! ጊዜ የለህም። አጅሬ መች እንደሚመጣ አይታወቅምና ካሁኑ ተዘጋጅ። ዛሬውኑ፤ ለነገ ምንም ዋስትና የለህማ! የእውቀት ማዕዶች በዙሪያህ ተጥደዋልና ተሽቀዳደም። አላህ ግዴታ ያደረገብህን ከሱናው፤ የከለከለህን ከተፈቀደው ለመለየት ቂርዐት ብቸኛ መንገድ ነውና ተጣደፍ። አልችልም እንዳትል፤ ትችላለህናአድርሰናል፤ አንተ/ቺም ሰምተሀ/ሻል!
رَبِّ هَبْ لِي حُكْمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ

ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ስጠኝ ከደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ፡፡” 26-83

No comments:

Post a Comment