መርየም ቢንት ዒምራን የጨዋነት ተምሳሌት ፡-
ስለዚህች እንቁ እንስት የነብዩ ዒሳ (ዐለይሂሰላም) እናት መርየም ጨዋነቷንና ጥብቅነቷን አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) በተከበረው ቃሉ ቁርአን ውስጥ በተደጋጋሚ አውስቶታል፡፡ ራሱን የቻለ ምእራፍ በስሟም ሰይሞላታል:: በእውነቱ ኢስላም ለሴት ልጅ ከሰጠው ክብርም ይህ በዋነኝነት ተጠቃሽ ነው:: ምክንያቱም በፈጣሪ ንግግር ውስጥ በክብር መወሳቷ የተፈጠረችለትን አላማ ይዛ ከተጔዘች ከመምጠቅና ከፍ ማለት የሚያግዳት ነገር እንደሌለ ያረጋግጣል፡፡የመርየምም ታሪክ ይህንን በጉልህ ያስቀምጣል::
አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ)እንዲህ ይላል:-
وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ مَرْيَمَ إِذِ انتَبَذَتْ مِنْ أَهْلِهَا مَكَانًا شَرْقِيًّا [١٦]فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا [١٧]قَالَتْ إِنِّي أَعُوذُ بِالرَّحْمَٰنِ مِنكَ إِن كُنتَ تَقِيًّا [١٨
«በመጽሐፉ ውስጥ መርየምንም ከቤተሰቧ ወደ ምሥራቃዊ ስፍራ በተለይች ጊዜ (የሆነውን ታሪኳን) አውሳ፡፡ ከእነሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ መንፈሳችንምም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡«እኔ ከአንተ በአልረሕማን እጠበቃለሁ፡፡ ጌታህን ፈሪ እንደ ሆንክ (አትቅረበኝ)» አለች፡፡´ (18:16-18)
እንግዲህ አንቺ ውዲቷ እህቴ ይህንን ገጠመኝ በጥሞና አስተንትኝው:: እጅግ በጣም ያማረ ውበት፣ የሰው ዘር ውልብ እንኴ የማይልበት ብቸኝነት፣ ታዲያ በዚህ አጔጊ እና ገፋፊ ሁኔታ ላይ በጣም ያማረና የተዋበ ሰው ከተፍ ሲል:: ምን ይፈጠራል ተብሎ መቼም አይጠየቅም ለማንም ግልጽ ነውና:: አጋጣሚው ተገኝቶ አደለም ሳይገኝ ለማግኘት እራሱ ስንት ከንቱ መስዋእትነቶች ይከፍላሉ፡፡ነገር ግን የተፈጠሩለትን አላማ በወጉ የተገነዘቡ ንጹህ የአላህ ባሮች ይህን ረመጥ ሳይቃጠሉ ይወጡታል:: ይህንንም ገድልከዚህች ብርቅዮ እንስት ታሪክ የምናገኘው ነው፡፡
by Ummu Abdellah Muhammed on Sunday, January 13, 2013 at 3:17pm
እንግዲህ አንቺ ውዲቷ እህቴ ይህንን ገጠመኝ በጥሞና አስተንትኝው:: እጅግ በጣም ያማረ ውበት፣ የሰው ዘር ውልብ እንኴ የማይልበት ብቸኝነት፣ ታዲያ በዚህ አጔጊ እና ገፋፊ ሁኔታ ላይ በጣም ያማረና የተዋበ ሰው ከተፍ ሲል:: ምን ይፈጠራል ተብሎ መቼም አይጠየቅም ለማንም ግልጽ ነውና:: አጋጣሚው ተገኝቶ አደለም ሳይገኝ ለማግኘት እራሱ ስንት ከንቱ መስዋእትነቶች ይከፍላሉ፡፡ነገር ግን የተፈጠሩለትን አላማ በወጉ የተገነዘቡ ንጹህ የአላህ ባሮች ይህን ረመጥ ሳይቃጠሉ ይወጡታል:: ይህንንም ገድልከዚህች ብርቅዮ እንስት ታሪክ የምናገኘው ነው፡፡
No comments:
Post a Comment